በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 9 ወራት ብቻ ከባድ ወንጀልን በ43 በመቶ መቀነስ መቻሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡
የጠቅላይ መምሪያው ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ጠቅላይ መምሪያው እያከናወነ ባለው የሪፎርም ስራ ከማህበረሰቡ ጋር የነበረውን ቅንጅታዊ ስራ እያጠናከረ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡
በዚህ የተቀናጀ ስራም ባለፉት 9 ወራት በቁጥጥር ስር ከዋሉ ወንጀል ፈፃሚዎች ውስጥ 65 በመቶ የሚሆኑት በህብረተሰቡ ተሳትፎ በቁጥጥር ስር የዋሉ መሆኑን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡
ወደ ፍርድ ቤት ሊያመሩ የሚችሉ ከ23 ሺህ በላይ አለመግባባቶችን ማህበረሰቡን ባሳተፈ ውይይት ማስማማትና ችግሩን መፍታት መቻሉንም ኮማንደር ማርቆስ ተናግረዋል፡፡
የከተማዋን እድገት የሚመጥን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ስልጡን የፖሊስ ሀይል በመገንባት ረገድ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ያመላከቱት ዳይሬክተሩ የስነ-ምግባር ግድፈት ያለባቸው ጥቂት የፖሊስ አባላትም በዲሲፒሊን እንዲጠየቁና አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው መደረጉን ጠቁመዋል ፡፡
በከተማዋ የሚከናወነው የኮሪደር ልማት ለወንጀል መቀነስ አይነተኛ ሚና መጫወቱን የሚናገሩት ኮማንደር ማርቆስ የሌባና ወንጀለኛ መደበቂያ የነበሩት የወንዝ ዳርቻዎች ነፃ መሆናቸውን በማሳያነት አቅርበዋል፡፡
በሽመልስ ታደሰ