በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ የሚገኝው ሁሉን አቀፍ ልማት ከተማዋን ለኑሮ ምቹ እና ለሌሎች የአፍሪካ ከተሞችም ተምሳሌት የሚሆን ነው ሲሉ የአፍሪካ የህጻናት ጥበቃ ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች ተናገሩ

You are currently viewing በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ የሚገኝው ሁሉን አቀፍ ልማት ከተማዋን ለኑሮ ምቹ እና ለሌሎች የአፍሪካ ከተሞችም ተምሳሌት የሚሆን ነው ሲሉ የአፍሪካ የህጻናት ጥበቃ ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች ተናገሩ

AMN-ሰኔ 14/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ የሚገኝው ሁሉን አቀፍ የከተማ ትራንስፎርሜሽን ልማት ከተማዋን ጽዱ እና ለኑሮ ምቹ የሚያደርግ ለሌሎች የአፍሪካ ከተሞችም ተምሳሌት የሚሆን ነው ሲሉ የአፍሪካ የህጻናት ጥበቃ ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡

ጥራት ያለውና አካታች የሆነን የህጻናት አስተደጋግ በአፍሪካ ለማምጣት የጋራ ትብብርን ማጠናከር በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የቆየው የአፍሪካ የህጻናት ጥበቃ ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ የተገነቡ ሁሉን አቀፍ የልማት ፕሮጀክቶች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

በልማት ፕሮጀክቶቹ በተለይ ህጻናት እና ታዳጊ ወጣቶችን ታሳቢ በማድረግ የተሰሩት ስራዎች ብሎም ከተማዋን ጽዱ ለማድረግ የተገነቡ የህዝብ መጸዳጃ ቤቶች እና ለአረንጓዴ ስፍራ እንዲሁም ለወንዝ ዳርቻ ልማት የተሰጠው ትኩረት የሚደነቅ መሆኑንም ነው ጎብኚዎቹ የተናገሩት፡፡

በልማት ስራዎቹ ለቅርስ ጥበቃ የተሰጠው ትኩረት እና የአድዋ ድል መታሰቢያን የመሳሰሉ የታሪክ እና የማንነት ኩራት የሆኑ ተግባራትን ለትውልድ ለማስተላለፍ የተሰራው ስራም የሚያኮራ መሆኑን ጎብኚዎቹ ገልጸዋል፡፡

የተከናወነው የልማት ስራ የህዝብ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች በቁርጠኝነት የመሩት መሆኑ ደግሞ ሌሎች የአፍሪካ ከተሞች በከተማ ልማት ረገድ ልምድ ሊወስዱበት የሚገባ መሆኑን ነው የጉብኝቱ ተሳታፊዎች የተናገሩት፡፡

በሰብስቤ ባዩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review