AMN – የካቲት 25/2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ የተሰሩ የልማት ስራዎች ከአሁኑ ትዉልድ ባለፈ ለመጭዉ ትዉልድ መደላድል የሚፈጥሩ መሆኑን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ኸይረድን ተዘራ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የመራጭ ተመራጭ የህዝብ ዉይይት እየተደረገ ነዉ፡፡

በመድረኩም የነበሩ የመልካም አስተዳደር ስራዎች እና የተከናወኑ የልማት ስራዎች ላይ እየተመከረ ይገኛል ፡
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ኒኢመተላህ ከበደ ባለፉት 3 ዓመታት የተከናወኑ ተግባራት ላይ ባቀረቡት ሪፖርት ተቋማትን እንደ አዲስ ማደራጀት ጨምሮ ምቹ የስራ አካባቢ ተፈጥሯል ብለዋል፡፡
ሰዉ ተኮር ተግባራት በማስፋፋት እና የመሰረተ ልማት አቅርቦትን በማስደግ የነዋሪውን የመልካም አስተዳደር ችግር ለመፍታት ስለ መስራቱም ወይዘሮ ኒኢመተላህ ከበደ ጠቁመዋል፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ኸይረድን ተዘራ፣ በከተማዋ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች እንደ ሀገር እና ከአሁኑ ትዉልድ ባለፈ ለመጭዉ ትዉልድ ትልቅ ተስፋን የሚሰንቅ እና መደላድል የሚፈጥር መሆኑን ገልፀዋል ::
በቴዎድሮስ ይሳ