በአዲስ አበባ የሚገኙ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች በመዲናዋ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎችን አደነቁ

You are currently viewing በአዲስ አበባ የሚገኙ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች በመዲናዋ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎችን አደነቁ

AMN- ሚያዝያ 25/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች የከተማዋን ገፅታ የቀየሩ እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን የሚጨምሩ መሆናቸውን በአዲስ አበባ የሚገኙ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት በአዲስ አበባ የተጠናቀቁ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው።

የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በአዲስ አበባ የዴሞክራሲ ስርአት ማስተባበርያ ማዕከል የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ አስተባባሪነት የካሳንቺስ የኮሪደር ልማትና የመልሶ ማልማት፣ የቦሌ ቡልቡላ ፓርክን ጨምሮ ሌሎች ቦታዎችን እየጎበኙ ይገኛሉ።

በጉብኝታቸውም የልማት ስራዎቹ ከጠበቁት በላይ ውበትና ጥራትን የተላበሱ፣ የከተማዋን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት በከፍተኛ ደረጃ የሚጨምሩ ከመሆናቸውም ባለፈ የነዋሪዎችን ኑሮ ደረጃን የሚያሻሽሉ ሆነው እንዳገኟቸው ተናግረዋል።

በተለይም መንግስት ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ የማጠናቀቅ አቅም የታየበት እና ጠንካራ የስራ ባህል የታየባቸው ስለመሆኑም ገልጸዋል።

በደሳለኝ ሙሀመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review