የአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ከመጋቢት 1 እስከ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ሲያካሂድ የቆየው የ5ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ሰነድ ሽያጭ የመክፈቻ መርሐ-ግብር ተካሂዷል።
በቦሌ ክፍለ ከተማ የተካሄደው 5ኛው ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ የመክፈቻ መርሐ-ግብር ለ5 ቀናት እንደሚቆይ ተገልጿል።
በአጠቃላይ 427 ፕሎቶች (የተዘጋጁ ቦታዎች) የተሰናዱበት 5ኛው ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ መካከል ዛሬ 86 ፕሎቶችን የያዙ 5 ክፍለ ከተሞች ማለትም፣ የካ ፣ ቂርቆስ ፣ ጉለሌ ፣ አራዳ እና ለሚ ኩራ ላይ ነው የተከፈተው።
በጨረታ መክፈቻው የአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሲሳይ ጌታቸውን ጨምሮ ሌሎች የቢሮው የስራ ኃላፊዎች፣ ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎች ተገኝተዋል።
በሄለን ጀንበሬ