በአዲስ አባባ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በትግራይ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ወይይት እያደረጉ ነው።
በመድረኩም በከተማዋ የሚኖሩ የክልሉ ተወላጆች ተገኝተዋል።
የፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነት የትግራይ ህዝብ ሰላም እንዲያገኝ ያደረገ ስምምነት ነው ሲሉ ጀነራል ዮሃንስ ገብረመስቀል ተናግረዋል።
በትግራይ የሚታዩ አንድ አንድ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ በተለያዩ አከባቢ ያሉ የክልሉ ተወላጆች የመፍትሔ አካል እንዲሆኑ ያስፈልጋል ሲሉም አክለው ተናግረዋል።
የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ይተግበር ማለት በክልሉ ያሉ የታጠቁ ሃይሎች ትጥቃቸውን ፈትተው ወደ ቀደመ ህይወታቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ነው ብለዋል።
በትግራይ ክልል ያሉ ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት መሰል ውይይቶች አስፈላጊ እንደሆነ የገለጹት ጀነራል ዮሃንስ እና ክልሉም መልሶ ወደ የማያስፈልግ ችግር እንዳይገባ የሁሉም ድርሻ ይጠይቃል ብለዋል።
በቀጣይ እንዲህ አይነቱ የመወያያና መመካከሪያ መድረኮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም የህዝቡ ድምጽ ሊያሰማ የሚችል የሲቪል አደረጃጀት እንደሚያስፈልግም አሳስበዋል።
በመድረኩ የተገኙ የምክክሩ ተሳታፊዎች በትግራይ ሰላም ለማስፈን መመካከር እንደሚያስፈልግ ገልፀው በሰላምና ልማት ላይ በትኩረት መሰራት እንዳለበት አስምሮበታል።
በእዮብ ርስቴ