የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ “ብቃት ያለው ሲቪል ሰርቪስ ለኢትዮጵያ ብልጽግና ” በሚል መሪ ሀሳብ ከወረዳ እስከ ከተማ ማዕከል ካሉ ተቋማት ከተውጣጡ የመንግሥት ሰራተኞች ተወካዮች ጋር በከተማዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚህ ውይይት እንግልት ይበዛባቸው በነበሩ ተቋማት የተሻለ አገልግሎት ማስፈን መቻሉን ተከትሎ ከህዝቡ ገንቢ አስተያየቶች እየተሰጡ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ይሁን እንጂ ጥቂት በሚሆኑ አገልጋዮች የሚፈጸም ሌብነትና ተገልጋዩን የማንገላታት ሁኔታ መኖራቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

ይህንን ችግር ለመከላከል አገልግሎትን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ ለውጥ ለማምጣት በተቀናጀ ሁኔታ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
በቀጣይም ሰራተኛው ተነቃቅቶ የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማስቻል
የተሻለ አፈጻጸም ለሚያስመዘግቡ ሰራተኞች ዕውቅና የመስጠት ስራ ይከናወናልም ብለዋል፡፡
ተሳታፊዎች በበኩላቸው የምዘና ስርአት ብሎም የኑሮ ውድነትና የመኖሪያ ቤት ችግሮቻቸው እንዲፈቱላቸው ጠይቀዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች የከተማ አስተዳደሩ የኑሮ ጫናን ለማቅለል በርካታ ድጋፎችን ማድረጉን አንስተዉ የመኖሪያ ቤትና የትራንስፖርት ድጎማ ብሎም የደመወዝ ጭማሪንም ከድጋፎቹ ተርታ አስቀምጠዋቸዋል በማብራሪያቸው፡፡

ከዚህ ባለፈ የኑሮ ውድነቱን ለማቅለል ምርት በገበያ ላይ በስፋት እንዲገባና በቸሻለ ዋጋ እንዲቀርብ ይሰራል ብለዋል፡፡
በአፈወርቅ አለሙ