በኢትዮጵያ ለተመዘገቡ ሁለንተናዊ እድገቶች የንግዱ ማህበረሰብ ሚና የጎላ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ

You are currently viewing በኢትዮጵያ ለተመዘገቡ ሁለንተናዊ እድገቶች የንግዱ ማህበረሰብ ሚና የጎላ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ

AMN ግንቦት – 27/2017ዓም

በኢትዮጵያ ለተመዘገቡ ሁለንተናዊ እድገቶች የንግዱ ማህበረሰብ ሚና የጎላ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ።

ሚኒስቴሩ “ለሁለንተናዊ ብልፅግና የንግዱ ማህበረሰብ ሚና” በሚል መሪ ሀሳብ ከንግዱ ማህብረሰብ ጋር እየመከረ ነው።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለጹት፣ መንግስት የሀገሪቱን ብልፅግና ለማረጋገጥ ብዝሀ ዘርፍ ኢኮኖሚ ልማትን ተግባራዊ በማድረግ በየዘርፉ ስኬቶችን እያስመዘገበ መሆኑን ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም በኢትዮጵያ ለተመዘገቡ ሁለንተናዊ እድገቶች የንግዱ ማህበረሰብ ሚና የጎላ መሆኑን ጠቅሰው፣ ለዘርፉ ተዋንያን ተገቢው እውቅና ይሰጣል ብለዋል።

የመንግስትና የግሉ ዘርፍ ትብብር በኢኮኖሚ የዳበረች ጠንካራ ሀገር ለመገንባት ወሳኝ መሆኑን በማንሳት፣ ግንኙነቱ በጠንካራ መሰረት ላይ መቀመጥ ይኖርበታል ብለዋል።

የንግዱን ዘርፍ ችግሮች በመፍታት ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ ሀገራዊ የንግድ ፖሊሲ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ከ63 ዓመታት በላይ የቆየው የንግድ ህግ እንዲሻሻል ተደርጓል ብለዋል።

በኢትዮጵያ ከስድስት ዓመታት በፊት ከሁለት ነጥብ ስድስት ቢሊየን በታች የነበረው የውጭ ንግድ ዘርፍ አፈፃፀም፣ በበጀት ዓመቱ አስር ወራት ብቻ ከስድስት ነጥብ ሁለት ቢሊየን ዶላር በላይ ማሳደግ መቻሉንም ሚኒስትሩ አመለክተዋል፡፡

ለኢትዮጵያ እድገትና ልማት የወጭ ንግድ ተወዳዳሪነት ወሳኝ መሆኑን በማንሳት የግሉ የንግድ ዘርፍ ተዋንያን የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ አሰራሮችን በማወቅ ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸውም ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

መንግስት ኢትዮጵያን የዓለም ንግድ ድርጅት አባል በማድረግ የንግዱን ማህበረሰብ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ በጊዜ የለኝም መንፈስ እየሰራ መሆኑን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review