በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ልደታ ክፍለ ከተማ ድሬዳዋ ከተማን አሸነፈ

You are currently viewing በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ልደታ ክፍለ ከተማ ድሬዳዋ ከተማን አሸነፈ

AMN – መጋቢት 1/2017 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ልደታ ክፍለ ከተማ ድሬዳዋ ከተማን አሸነፏል፡፡

የ14ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በተደረጉ 2 ጨዋታዎች ሲጠናቀቁ ልደታ ክፍለ ከተማ ድሬዳዋ ከተማን 1ለ0 ማሸነፍ ችለዋል።

የጨዋታው ኮከብ መሆን የቻለችው ገብሬላ አበበ ልደታን አሸናፊ ያደረገች ብቸኛ ግብ በ75 ደቂቃ ከመረብ አሳርፋለች።

በሌላ ጨዋታ የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከመቻል ያደረጉት ጨዋታ 0ለ0 በሆነ የአቻ ውጤት ተጠናቋል።

ተመጣጣኝ ፋክክር በተደረገበት ጨዋታ ሁለቱ ቡድኖች ግብ ለማስቆጠር ያደረጉት ሙከራ ሳይሳካላቸው ቀርቷል።

ሊጉን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ38 ነጥብ ሲመራ ሀዋሳ ከተማና ሲዳማ ቡና በግብ ክፍያ ተበላልጠው በእኩል 26 ነጥብ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል ።

ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ቂርቆስ ክፍለ ከተማና ሀምበሪቾ ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኙ ክለቦች ናቸው ።

በሀና ታሪኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review