በኢትዮጵያ – አዲስ አበባ ታምርት ንቅናቄ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ችግር መፍታት ተችሏል-አቶ ጃንጥራር አባይ

You are currently viewing በኢትዮጵያ – አዲስ አበባ ታምርት ንቅናቄ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ችግር መፍታት ተችሏል-አቶ ጃንጥራር አባይ

AMN-መጋቢት 5/2017 ዓ.ም

በኢትዮጵያ – አዲስ አበባ ታምርት ንቅናቄ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ችግር መፍታት መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ገለፁ።

ኃላፊው በከተማ አቀፍ ደረጃ በሚከናወነዉ ኢትዮጵያ -አዲስ አበባ ታምርት ንቅናቄ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ ከክፍለ ከተማ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና አስተባባሪዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

አቶ ጃንጥራር አባይ፣ በኢትዮጵያ -አዲስ አበባ ታምርት ንቅናቄ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ችግር መፍታት እንደተቻለ ገለጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ -አዲስ አበባ ታምርት ንቅናቄ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ሲካሄድ እንደቆየ ያስታወሱት ምክትል ከንቲባዉ በንቅናቄዉ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የመሰረተ ልማት ችግር መፍታት እንደተቻለ ጠቁመዋል፡፡

የንቅናቄ መድረኩ በቀጣይ በከተማ አቀፍ ደረጃ የፌደራል እና የከተማ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ እንደሚከናወን ገልጸዋል።

በዕለቱ በርካታ አምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶች የሚሳተፉበት ኤግዚቢሽን እና ባዛር አዉደ ርዕይ እንደሚካሄድ ጠቁመዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ የመስሪያ እና የማስፋፊያ ቦታ ጥያቄ ላቀረቡ አምራች ኢንዱስትሪዎች ተገቢዉን ጥናት በማድረግ እና ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመቀናጀት ምላሽ መስጠት እንደተቻለም አቶ ጃንጥራር ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ -አዲስ አበባ ታምርት ንቅናቄ ከመጋቢት 29- ሚያዚያ 4 ቀን ለተከታታይ አምስት ቀናት እንደሚካሄድ የቢሮው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review