በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የፈጠራ ውጤቶች የክህሎት ባንክ ተከፈተ

You are currently viewing በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የፈጠራ ውጤቶች የክህሎት ባንክ ተከፈተ

AMN – ሚያዚያ 1/2017

በሰመር ካምፕ እና በክህሎት ኢትዮጵያ መርኃ ግብር የተሰሩ የፈጠራ ውጤቶች የክህሎት ባንክ ተከፍቷል።

የክህሎት ባንኩን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል መርቀው ከፍተውታል።

በክህሎት ባንኩ የሚገኙት የፈጠራ ውጤቶች ባለፈው ዓመት የሰመር ካምፕ ፕሮግራም እንዲሁም በዘንድሮ የክህሎት ኢትዮጵያ ተሳታፊዎች የተሰሩ እና እየተሰሩ ያሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ናቸው።

ይህ በፌዴራል የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የሚገኘው የክህሎት ባንክ የቴክኖሎጂ ባለቤቶችን የፈጠራ ምርቶችን መጠቀምና ማስመረት ከሚፈልጉ ደንበኞች ጋር የሚያገናኝ ነው መሆኑ ተገልጿል።

ባንኩ ለጎብኚዎች ክፍት ሲሆን የመንግስት እና የግል ሴክተሮች የፈጠራ ውጤቶችን በመጎብኘት እንዲመረትላቸው የሚፈልጓቸውን ምርት ትዕዛዝ መስጠት የሚችሉበት ምቹ ሁኔታ መኖሩም ተገልጿል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ለ21 ኢንተርፕራይዞች ያዘጋጀው የመስሪያ ቦታ ርክክብ መደረጉን ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review