በኢትዮጵያ ጉዳይ ለጋራ ግብ የሚቆም ትውልድ ለመገንባት አሰባሳቢ ትርክት አይተኬ ሚና እንደሚጫወት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ

You are currently viewing በኢትዮጵያ ጉዳይ ለጋራ ግብ የሚቆም ትውልድ ለመገንባት አሰባሳቢ ትርክት አይተኬ ሚና እንደሚጫወት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ

AMN ግንቦት 29/2017

በኢትዮጵያ ጉዳይ ለጋራ ግብ የሚቆም ትውልድ ለመገንባት አሰባሳቢ ትርክት አይተኬ ሚና እንደሚጫወት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ በለውጡ ማግስት የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት የተመዘገቡ ስኬቶችንና የታለፉ ተግዳሮቶችን በማስመልከት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር የትርክት ግንባታ ላይ ትኩረት መስጠትና ትርክትን በወጉ መገንዘብ ጠቃሚ ነው ብለዋል።

በአሸናፊና ተሸናፊ ሥነ-ልቦና የተሞላው የዕለት ከዕለት አላስፈላጊ የውድድር ውሏችን የትርክት ውጤት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ነጣጣይ ትርክቶች ጉዳታቸው ከፍተኛ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ትርክት ግለሰብ፣ ማኅበረሰብና ሀገር የሚገነባበት መሰረታዊ ምሰሶ መሆኑን በማንሳት፥ በኢትዮጵያ ጉዳይ ለጋራ ግብ የሚቆም ትውልድ ለመገንባት አሰባሳቢ ትርክት አይተኬ ሚና አለው ነው ያሉት።

በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ አሉታዊ እሳቤን የሚያራምዱ ልሂቃን ከፋፋይ ትርክት በማስረጽ የዕርስ በእርስ መጠራጠር እንዲፈጠር መንገድ እየከፈቱ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።

ኢትዮጵያን ከድህነት የሚያወጣት፣ ብልጽግናዋን የሚያረጋግጥ ተቋም መገንባትና በጋራ መኖር የሚያስችል አሰባሳቢ ትርክት እንደሚያስፈልግ ገልጸው፥ መንግሥት አሰባሳቢ ትርክት ላይ እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

ብሔራዊ ጥቅምንና ህብረ ብሔራዊ አንድነትን መሰረት ያደረገ ገዥ ትርክት መገንባት እንደሚገባም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አፅንኦት ሰጥተዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review