ባለፉት ዘጠኝ ወራት በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት እና በኃይል አቅርቦት ላይ በተፈፀ ስርቆት እና ቆጣሪዎች ስራ እንዳይሰሩ በማወክ 199 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ጉዳት መድረሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለኤ አም ኤን አስታውቋል፡፡
ከዚህ ውስጥ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ብቻ በተፈፀመ ጉዳትና ስርቆት 52 ሚሊዮን 33 ሺህ 123 ብር የሚገመት የገንዘብ ጉዳት በተቋሙ ላይ መድረሱን አገልግሎቱ አመላክቷል፡፡
አገልግሎቱ የስርቆትና መሰል ወንጀሎችን በፈፀሙ 208 ግለሰቦች ላይ የክስ መዝገቦችን ከፍቶ፣ በ27 መዝገቦች ላይ ውሳኔ እንዲሰጥ በማድረግ ወንጀለኞቹ ከ2 ወር እስከ 10 አመታት በሚደርስ ፅኑ እስራት እና ከ25 ሺህ እስከ 50 ሺህ ብር የሚደረስ የገንዘብ ቅጣት እንደተላለፈባቸው ገልጿል፡፡
በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈፀም ማንኛውም ጉዳት እና ስርቆት በሀገር ላይ አሉታዊ ተፅእኖ የሚያስከትል ስለሆነ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን በመጠበቅ ረገድ እያንዳንዱ ዜጋ ሀላፊነቱን እንዲወጣም አገልግሎቱ አሳስቧል፡፡
በተለይም የፀጥታው ዘርፍ እና ሚዲያዎች ህብረተሰቡን እና ባለድርሻ አካላትን የማስገንዘብና የማንቃት ሚና እንዲወጡ አገልግሎቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡
በአስማረ መኮንን