በእስራኤል-ኢራኑ ጦርነት በመካከለኛው ምስራቅ ልላ ኪሳራ ሊገጥመኝ ይችላል-ሩሲያ

You are currently viewing በእስራኤል-ኢራኑ ጦርነት በመካከለኛው ምስራቅ ልላ ኪሳራ ሊገጥመኝ ይችላል-ሩሲያ

AMN – ሰኔ 11/2017 ዓ.ም

እስራኤል የአንበሳ መነሳት ዘመቻን ስትጀምር የሩሲያ ባለስልጣናት በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ አሳሳቢ እና አደገኛ ሲሉ ገልፀውታል።

እንደዛም ሆኖ የሩሲያ ሚዲያዎች ለሞስኮ ያለውን አዎንታዊ ውጤት አፅንዖት ለመስጠት አልዘገዩም።

ከአዎንታዊ ውጤቶቹ መካከል የሩስያን ካዝና እንደሚያሳድግ የተተነበየለት የአለም የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ የመጀመሪያው ነው።

በትኩረት መከፈል ምክንያት የአለም አይኖች ከሩሲያና ዪክሬን ላይ መነሳት ሌላው የተጠቀሰ ጉዳይ ሲሆን ይህንንም ለማመላከት የሩሲያ እውቅ ጋዜጣ ”ኬቭ ተረሳ” በማለት የፊት ገፁ ላይ አትሟል።

በተጨማሪም ክሬምሊን እስራኤልን እና ኢራንን ለማስታረቅ ያቀረበው ሀሳብ ተቀባይነት ካገኘ ሩሲያ ራሷን በመካከለኛው ምስራቅ እንደ ቁልፍ ተዋናይ እና ሰላም ፈጣሪ ማሳየት መቻሏ አንዱ በጎ ጎን ነው በማለት የሩሲያ መገናኛ ብዙሃን መጥቀሳቸውን ቢቢሲ ዘግቧል ።

ግጭቱ በዚሁ ከቀጠለ ግን ሩሲያ በብዙ እንደምትከስር የሩሲያ ባለስልጣናት አመላክተዋል።

ከወራት በፊት ሩሲያ እና ኢራን የአጋርነት ስምምነት መፈራረማቸው የሚታወስ ሲሆን ስምምነቱ ወታደራዊ ስምምነትን የሚያካትት አለመሆኑና ኢራንን ከጥቃት መከላከል አለመቻሏ ሩሲያ በመካከለኛው ምስራቅ አለኝ የምትለውን አጋር ሊያሳጣት እንደሚችል ያላትን ስጋት መግለጿ በዘገባው ተመላክቷል።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review