
AMN-ግንቦት 7/2017 ዓ.ም
የውድድር ዓመቱ መገባደጃ ላይ የሚገኘው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ለመምረጥ ስምንት እጩዎችን አቅርቧል፡፡
ከስምንቱ እጩዎች ውስጥ ሊቨርፑል ሞሃመድ ሳላህ ፤ ቨርጅል ቫንዳይክ እና ሪያን ግርቨንበርችን በማስመረጥ ቅድሚያውን ወስዷል፡፡
የኖቲንግሃም ፎረስቶቹ ሞርጋን ጊብስ ኋይት እና ክሪስ ዉድ ፤ ዴክለን ራይስ ከአርሰናል ፤ አሌክሳንደር ኢሳክ ከኒውካስትል እንዲሁም ብሪያን ምቤሞ ከብሬንትፎርድ ሌሎች እጩዎች ናቸው፡፡
በተመሳሳይ የአሰልጣኞችም እጩዎች ይፋ ሆነዋል፡፡

በዚህም አርነ ስሎት ከሊቨርፑል ፤ ኤዲ ሃው ከኒውካስትል ዩናይትድ ፤ ቶማስ ፍራንክ ከ ብሬንትፎርድ ፤ ኑኖ ስፕሪቶ ሳንቶ ከኖቲንግሃም ፎረስት እንዲሁም ቪቶር ፔሬራ ከወልቭስ በእጩነት የቀረቡ አሰልጣኞች ናቸው፡፡
በሸዋንግዛው ግርማ