በኦሮሚያ ክልል እየተከናወነ የሚገኘው የከተሞች የኮሪደር ልማት ፍትሃዊ ልማትን የሚያረጋግጥ ነው

You are currently viewing በኦሮሚያ ክልል እየተከናወነ የሚገኘው የከተሞች የኮሪደር ልማት ፍትሃዊ ልማትን የሚያረጋግጥ ነው

በኦሮሚያ ክልል እየተከናወነ የሚገኘው የከተሞች የኮሪደር ልማት ፍትሃዊ ልማትን የሚያረጋግጥ ነው

AMN – ሚያዚያ 09/2017 ዓ.ም

በኦሮሚያ ክልል እየተከናወነ የሚገኘው የከተሞች የኮሪደር ልማት ፍትሃዊ ልማት ለዜጎች እንዲደርስ እድል መፍጠሩን የክልሉ ከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ገለጸ።

የኦሮሚያ ከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ብርሃኑ በቀለ እንደገለጹት በክልሉ በሚገኙ 732 ከተሞች የኮሪደር ልማት ስራ እየተከናወነ ይገኛል።
የኮሪደር ልማት ስራው ዋና አላማ በከተሞች መሰረተ ልማትን በተቀናጀ መልኩ ማስፋፋት፣ የከተሞችን ፕላን በዘመናዊ እና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ማዘጋጀት እና ለሌሎችም መሆኑን አስታውሰዋል።

በኮሪደር ልማት ስራው ያሉትን የትራንስፖርት አማራጮች ለማስፋት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው በኮሪደር ልማቱ የከተማን ውበት ለማጎልበት በርካታ አጋዥ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review