የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አወሉ አብዲ ፕሮጀክቶቹን አስመልክተው ለመገናኛ ብዙሀን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ምክትል ፕሬዝዳንቱ በዘንድሮ በጀት ዓመት በኦሮሚያ ክልል ከ27 ሺህ በላይ አዲስና ነባር ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት ይደረጋሉ ብለዋል፡፡
ፕሮጀክቶቹ ከ200 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው መሆኑን ገልፀው በመንግሥት፣ በሕብረተሰብ ተሳትፎና በአጋር አካላት ትብብር መጠናቀቃቸውንም ተናግረዋል፡፡
እነዚህ የተጠናቀቁት ፕሮጀክቶች ከ45 ሚሊየን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርጉም አክለዋል፡፡
ፕሮጀክቶቹ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 የመጀመሪያው ዙር እንዲሁም እስከ ሐምሌ አጋማሽ 2ኛው ዙር ምረቃ ተከናውኖ አገልግሎት እንደሚጀምሩ አቶ አወሉ በመግለጫቸው አብራርተዋል፡፡
በመሀመድኑር አሊ