
AMN-ታህሳስ 7//2017 ዓም
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ማካሄድ ጀምሯል።
የምክክር መድረኩ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም ተካሂዷል።
በማስጀመሪያ መርሃግብሩ ላይ ከ7 ሺህ በላይ የምክክሩ ተሳታፊዎች ፣ የሃይማኖት አባቶች እና አባገዳዎችን ጨምሮ የተለያዩ እንግዶች ተገኝተዋል።
ከታህሳስ 7 እስከ 15 በሚቆየው የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ተሳታፊዎች አነስተኛ ቡድኖች ተከፋፍለው በመወያየት ሀገራዊ መግባባት ሊደረሰባቸው ይገባል ያሏቸውን የጋራ አጀንዳዎች ለኮሚሽኑ የሚያቀርቡ ይሆናል።
በካሳሁን አንዱአለም