በኦሮሚያ ክልል የከተማ እና የገጠር ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደረጉ የንጹህ መጠጥ ውሃ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተገነቡ መሆናቸዉ ተገለጸ

You are currently viewing በኦሮሚያ ክልል የከተማ እና የገጠር ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደረጉ የንጹህ መጠጥ ውሃ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተገነቡ መሆናቸዉ ተገለጸ

AMN – ግንቦት 20/2017 ዓ.ም

በኦሮሚያ ክልል የከተማ እና የገጠር ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደረጉ የንጹህ መጠጥ ውሃ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተገነቡ መሆናቸዉ ተገልጿል፡፡

የኦሮሚያ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ከኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ጋር በመተባበር በተለያዩ የአርሲ እና የባሌ ዞኖች እና ወረዳዎች የተሠሩ የውሃ መሰረተ ልማት ስራዎችን ለመገናኛ ብዙሃን እና ለኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች እያስጎበኘ ይገኛል።

በጉብኝቱም የሄበን ነገሌ ሲራሮ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ስራ አሰኪያጅ ኢንጂነር አልዬ አንግሾ በሰጡት ገለጻ፣ በምዕራብ አርሲ ዞን በተለይም በሄበን ነገሌ ሲራሮ በተሰራ ስራ ሁሉንም የአካባቢው ነዋሪዎች የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

የኦሮሚያ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ የኮሙኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ መስፍን ተስፋዬ በበኩላቸው፣ የክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ በለውጡ አመታት በተሰሩ የሪፎርም ስራዎች የከተማ ነዋሪውንና የገጠር አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ያደረጉ ተጨባጭ የንጹህ መጠጥ ውሃ መሰረተ ልማት ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።

ከመኖሪያ ቤት በተጨማሪም በጤና እና በትምህርት ተቋማት፣ በተለያዩ የንግድ ድርጅቶች ጭምር የንጹህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት እንዲዳረስ ስለመደረጉ ዳይሬክተሩ አብራርተዋል፡፡

የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እና የክልሉ የውሃና ኢነርጂ ቢሮ አመራሮች እንዲሁም በየደረጃው ያሉ የዘርፉ አመራሮችና ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈው የመስክ ጉብኝት እንደቀጠለ ነው።

በምትኩ ተሾመ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review