የአየር መንገድ ሰራተኞች በከተማዋ የተገነቡ እና በመገንባት ላይ ያሉ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
የአየር መንገድ ሰራተኞች በስራ አጋጣሚ በተለያዩ የዓለም ሀገራት እናያቸው የነበሩ የልማት ስራዎች በሀገራችን መስራት እንደሚቻል ያየንበት ነው ብለዋል።
የአየር መንገድ ሰራተኞች በአጭር ጊዜ የተገነቡ የልማት ስራዎች የከተማዋን ውበት ከመጨመር ባሻገር ለትውልድ የሚሻገሩ ስራዎች መሰራታቸውን በተጨባጭ አይተናል ብለዋል።
መንግስት እያከናወናቸው ያሉት ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች በትውልድ ግንባታ ላይ የራሳቸው በጎ ሚና እንዳላቸው የገለፁት የአየር መንገድ ሰራተኞች፣ ይህንን መልካም ጅማሮ ማስቀጠል ከትውልዱ ይጠበቃል ብለዋል።
የጉብኝት መርሐ-ግብሩም የአዲስ አበባ ከተማ የማህበራዊ ትረስት ፈንድ ጽሕፈት ቤት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ መሆኑ ተመላክቷል።
በመሀመድኑር አሊ