የኪነጥበብ ባለሙያዎቹ በአዲስ አበባ የተከናወኑ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ያዘጋጀው ጉብኝት ታዋቂ አርቲስቶች ፤ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ፤ ባለ ልዩ ተሰጥኦ ባለቤቶች እና አንጋፋና ወጣት የኪነጥበብ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል::
ጎብኝዎቹም በከተማዋ በተለያዩ ቦታዎች የተገነቡ ሰው ተኮር የልማት ስራዎች መጪውን ትውልድ የሚመጥኑ የነዋሪውን የመሠረተ ልማት ጥያቄዎችን የመለሱ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
እየተተገበሩ ያሉ የልማት ስራዎች የከተማዋን ብሎም የሃገሪቱን የቱሪስት መዳረሻነት ያሳደጉ ፤ ከተማዋን በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እና ተመራጭ እንድትሆን ያስቻሉ ናቸው ብለዋል::
የከተማ አስተዳደሩ የነዋሪችን የልማት ጥያቄ ለመመለስና የሀገርን ገጽታ ለመገንባት የሚያከናውናቸው ተግባራት ከግብ እንዲደርሱ የዘርፉ ባለሙያዎች የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል ሲሉ በጉብኝቱ የተሳተፉ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡
በታምሩ ደምሴ





See insights and ads
All reactions:
6767