በካሳንችስ ካምፕ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ የፖሊስ አባላት በልዩ ሁኔታ ምትክ የመኖሪያ ቤት እጣ አወጡ

AMN ህዳር 23/2017 ዓ.ም

በካሳንችስ አካባቢ በካምፕ ውስጥ ከቤተሰብ ጋር ይኖሩ የነበሩ የፖሊስ አባላት ካምፑ በመልሶ ማልማት በመነሳቱ በልዩ ሁኔታ ምትክ የመኖሪያ ቤት እጣ አወጡ፡፡

የከተማ እድገትን ከዜጎች ተጠቃሚነት ጋር አቀናጅታ በልማት ጎዳና ወደ ፊት እየተራመደች ያለችዉ አዲስ አበባ ከተማ ሁለተኛዉ ዙር የኮሪደር ልማትን በፍጥነት እና በጥራት እያከናወነች መሆኑ ይታወቃል ፡፡

መዲናዋ የኮሪደር ልማቱ በሚርስባቸው አካባቢዎች በልማት ለሚነሱ ዜጎችም ክብርን የሚመጥን እና ለዘመናዊ አኗኗር ምቹ የሆኑ ቤቶችን እና ምትክ ቦታዎችን የማስረከብ ስራም ጎን ለጎን እያካሄደች ትገኛለች፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ልማት እና አስተዳዳር ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ቅድስት ወልደጊዮርጊስ ምትክ ቤት የተሠጣችው የጸጥታ አካላት ምቹ ባልሆነ ሁኔታ ዉስጥ በካምፕ ዉስጥ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ይኖሩ የነበሩ ስለመሆኑ ተናገረዋል ፡፡

ለሀገር እድገት እና ለከተማ ልማት የማይተካ ሚናን የሚወጡት እነዚህ የፖሊስ አባላት በመዲናዋ እድገት ላይ የሚያበረክቱት ድርሻ የጎላ ስለመሆኑ ፖሊሶቹ ተናግረዋል ፡፡

የቤት ዕጣ ማዉጣት ስነ ስርዐቱም ግልፅና ፍትሀዊ እንደነበር ጠቁመዋል ፡፡

በካምፕ ውስጥ ከቤተሰብ ጋር ለመኖር ምቹ አለመሆኑን ያወሱት በልዩ ሁኔታ እጣ ያወጡት የፖሊስ አባላቱ ዛሬ እጣ በማውጣታቸው ችግራቸው ሙሉ በሙሉ እንደሚቀረፍ ገልፀዋል ፡፡

ከተማ አስተዳደሩ ለፖሊስ አባላቱ በሰጠዉ ትኩረት ምቹ የመኖሪያ ቤትን በምትክነት በማግኘታቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል ፡፡

በተመስገን ይመር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review