በኬንያ በ18 የተለያዩ እስር ቤቶች የነበሩ 287 ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

You are currently viewing በኬንያ በ18 የተለያዩ እስር ቤቶች የነበሩ 287 ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

AMN – የካቲት 26/2017 ዓ.ም

በህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ተታለው በኬንያ ሞያሌ ድንበር አቋርጠው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሻገር ሲሞክሩ በኬንያ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው በኬንያ በ18 የተለያዩ እስር ቤቶች የነበሩ 287 ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ሚሲዮኑ ከኬንያ የወንጀል ምርመራ ቢሮ (ዲሲአይ)፣ ከኬንያ ብሔራዊ የፖሊስ አገልግሎት እና ከኬንያ ኢሚግሬሽን ቢሮ ጋር በመተባበር ባሉበት እስር ቤት በአካል በመገኘት ጉብኝት ማካሄዱም ተመላክቷል፡፡

በዚህም በአስቸኳይ በኬንያ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ በማድረግ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ሥራ መሰራቱ ተገልጿል፡፡

በተከናወነው ስራም በዛሬው ዕለት በአጠቃላይ 287 ኢትዮጵያዊያን በየብስ ትራንስፖርት በሞያሌ ድንበር ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን ከኬኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review