በኬንያ የባሕር ዳርቻ ማሊንዲ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ የሦስት ሰዎች ሕይወት አለፈ

AMN – ጥር 3/2017 ዓ.ም

በኬንያ የባሕር ዳርቻ ማሊንዲ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአካባቢው ባለ ሥልጣናት ገለጹ።

ከፍተኛ የትራፊክ እንቅስቃሴ በሚበዛበት ሞምባሳ አውራ ጎዳና ላይ ከአውሮፕላን ማረፊያው ጥቂት ሜትሮች ርቃ በምትገኘው ክዋቾቻ የተሰኘች አነስተኛ ከተማ ነው የቀላል አውሮፕላን መከስከሱ ያጋጠመው፡፡

የኣይን እማኞች አውሮፕላኑ ሲከሰከስ በስብርባሪው ተላላፊ መንገደኞችን መምታቱንና በእሳት መያያዙን ገልጸዋል።

ባለሥልጣናት የአደጋው ሰለባዎች በእሳት ተቃጥሎ ህይወቱ ያለፈ የሞተር ብስክሌት ጋላቢና በአውሮፕላኑ የተወሰነ ክፍል ስብርባሪ ተመትተው ህይወታቸው ያለፈ ሌሎች ሁለት ሰዎች ናቸው ብለዋል።

የአውሮፕላኑ አብራሪ እና ተሳፋሪ የነበሩ ሁለት ተማሪዎች ከአደጋው በፊት ከአውሮፕላኑ ለመዝለል ባደረጉት ሙከራ ባጋጠማቸው ጉዳት ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑ ተነግሯል፡፡

ፖሊስ የአደጋውን መንስኤ እየመረመረ ነው መባሉን አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review