በክፍለ ከተማው ከለውጡ በኋላ የቆዩ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ መደረጉ ተመላከተ

You are currently viewing በክፍለ ከተማው ከለውጡ በኋላ የቆዩ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ መደረጉ ተመላከተ

AMN- ግንቦት 19/2017 ዓ.ም

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ለዘመናት ምላሽ ሳያገኙ የቆዩ የመልካም አስተዳደር እና የልማት ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ መደረጉን የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና አስገንዝበዋል፡፡

ክፍለ ከተማው በአገልጋዩ እና በእንጠያየቅ መድረክ የተነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እና ምላሽ በተሰጠባቸው ጉዳዮች ላይ እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት በሚሹ የልማት ስራዎች ላይ ምክክር እያደረገ ነው፡፡

ከለውጡ በፊት የክፍለ ከተማው ነዋሪ በርካታ ጥያቄዎች ነበሩት ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው፣ ከለውጡ በኋላ የመልካም አስተዳደር እና የልማት ስራዎች ቅድሚያ በመስጠት መፍታት መቻሉን ተናግረዋል ::

ምላሾቹም ለበርካቶች የስራ ዕድል የፈጠሩ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ መሆናቸውንም ስራ አስፈፃሚው ተናግረዋል ::

ከመልካም አስተዳዳር እና ከአገልግሎት አስጣጥ ጋር ተያይዞ ይነሱ የነበሩ ጥያቄዎች ለመመለስም በርካታ አገልግሎቶችን ዲጂታል ማድረግ ተችሏል ብለዋል ::

በቴዎድሮስ ይሳ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review