AMN-የካቲት 19/2017 ዓ.ም
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 2 ካራ ቆሬ በተለምዶ ቢቂላ መናፈሻ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ለፍራሽ መስሪያ የሚሆኑ ግብአቶች በተከማቹበት መጋዘን ላይ የተከሰተው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገልጿል።
በዛሬው ዕለት ከቀኑ 9:33 ሰዓት ላይ የተከሰተውን የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እና የጸጥታ አካላት እንዲሁም የአካባቢዉ ህብረተሰብ ባደረጉት ርብርብ እሳቱ በአቅራቢያ ወዳሉ መስኪድ እና ሌሎች መኖሪያ እና ንግድ ቤቶች እንዳይዛመት ማድረግ መቻሉንም ኮሚሽኑ አመላክቷል።
በእሳት አደጋዉ በሰዉ ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩንም ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለእሳት እና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ እዲያሳዉቁም ጥሪ አቅርቧል፡፡