AMN-መጋቢት 11/2017 ዓ.ም
በኮሪደር ልማቱ ለተነሱ ዜጎች ከ17 ቢሊዮን ብር በላይ ካሳ መከፈሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምክር ቤት አባላት በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ
የኮሪደር ልማት ከዛሬ ባሻገር ቀጣዩ ትውልድን መሰረት ያደረገ ነው ብለዋል::

በአዲስ አበባ ብቻ በኮሪደር ልማት አማካኝነት ከ200 ኪሎሜትር በላይ መንገድ መሰራቱን ተናግረዋል፡፡
እንዲሁም ሰፋፊ የእግረኛ መንገዶችም መከናወናቸውን ጠቁመዋል።
በኮሪደር ልማቱ ለተነሱ ዜጎችም በቂ ካሳ መከፈሉን ያወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እስካሁን ባለው ሂደትም ከ17 ቢሊዮን ብር በላይ ካሳ ተከፍሏል ነው ያሉት።
በኮሪደር ልማት በሁሉም የክልል ከተሞች አስደማሚ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡