በኮሪደር ልማቱ የተሰሩ የተለያዩ መሰረተ ልማቶች ለታለመላቸው አላማ እንዲውሉ በተቋማት የተሰሩ ስራዎች አበረታች ናቸው-የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን

  • Post category:ልማት

AMN – ታኀሣሥ 3/2017 ዓ.ም

በኮሪደር ልማቱ የተሰሩ የተለያዩ መሰረተ ልማቶች ለታለመላቸው አላማ እንዲውሉ በተቋማት የተሰሩ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተረ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት የኮሪደር ልማት ስራዎችን በተመለከተ በቅንጅት ለመስራት የተፈራረሙት የደንብ ማስከበር ባለስልጣን፣የግንባታ ፈቃድና እና ቁጥጥር ባለስልጣን፣ የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ፣የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን እና የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን በ5 ወራት ውስጥ በቅንጅት የተሰሩ ስራዎችን ገምግመዋል።

ባለፉት ወራት ተቋማቱ በኮሪደር ልማቱ የተሰሩ የተለያዩ መሰረተ ልማቶች ለታለመላቸው አላማ እንዲውሉ ማድረግ መቻላቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተረ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ተናግረዋል።

የሚከሰቱ የደንብ መተላለፎችን በመከላከል ረገድ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ መፍጠር መቻሉም ተመላክቷል፡፡

የኮሪደር መሰረተ ልማትን በተቀናጀ ሁኔታ በመጠበቅ የደንብ መተላለፍ እና ተያያዥ ህገወጥ ተግባራት በከተማዋ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ ተፅዕኖ እንዳያሳድሩ ተቋማቱ በጋራ እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል።

በፊርደውስ አብዱልሐኪም

All reactions:

5656

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review