በዓሉን ስናከብር የተከፈለልንን የፍቅር ዋጋን በማሰብ በአቅማችን በመረዳዳት እና በመተሳሰብ ይሁን-ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው

You are currently viewing በዓሉን ስናከብር የተከፈለልንን የፍቅር ዋጋን በማሰብ በአቅማችን በመረዳዳት እና በመተሳሰብ ይሁን-ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው

AMN – ሚያዝያ 11/2017 ዓ.ም

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል ፡፡

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ በየአመቱ የምናከብረው የትንሳኤ በዓል ጌታችንና መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ደህንነት እስከ መስቀል ሞት ታዞ፣ሞትን አሸንፎ ፣የሰውን ልጆቸ በሙሉ ወደ ብርሀን ያሻገረበት ታላቅ በዓል ነው ብለዋል፡፡

በዓሉን ስናከብርም የተከፈለልንን የፍቅር ዋጋን በማሰብ ድጋፍ ለሚሹ ሕጻናት፣አረጋውያን እና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች በአቅማችን በመረዳዳት እና በመተሳሰብ ይሁን ብለዋል፡፡

በዓሉ የሰላም፣የፍቅር እና የአብሮነት እንዲሆንም ተመኝተዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review