AMN – ታኅሣሥ 28/2017 ዓ.ም
በዓልን ምክንያት በማድረግ እየተከናወነ ያለው የማእድ ማጋራት መርሀ ግብር ባህል እየሆነ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ገለጹ፡፡
ቢሮው የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ ለሰራተኞቹ ማዕድ አጋርቷል ፡፡
በዓልን ምክንያት በማድረግ እየተከናወነ ያለው የማእድ ማጋራት መርሀ ግብር ባህል እየሆነ ስለመምጣቱ የገለጹት አቶ ጃንጥራር አባይ መርህ ግብሩ ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል እንኳን አደረሳችሁ ከማለት ጎን ለጎን አብሮነትንና መተሳሰብን የማጎልበቻ መንገድ ነውም ብለዋል ፡፡
ቢሮው በየአመቱ ማእድ የማጋራት መርሀ ግብር እንደሚያደርግ የገለጹት የቢሮው ሰራተኞች ይህ መተሳሰብንና ኢትዮጵያዊ ባህልን የሚያጠናክር በመሆኑ እነሱም በዓልን አቅም ከሌላቸው ጋር በመጋራት ያላቸውን በማካፈል እንደሚያሳልፉ ገልጸዋል ፡፡
በጽዮን ማሞ