በዘጠኝ ቀናት ከ7 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎች ላይ ድንገተኛ ፍተሻ መካሄዱ ተገለጸ

You are currently viewing በዘጠኝ ቀናት ከ7 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎች ላይ ድንገተኛ ፍተሻ መካሄዱ ተገለጸ

AMN – መጋቢት 30/2017 ዓ.ም

በዘጠኝ ቀናት ውስጥ 7 ሺህ 051 ተሽከርካሪዎች ላይ ድንገተኛ ፍተሻ መካሄዱን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ገልጿል።

በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እና ባለድርሻ አካላት ቅንጅት የተካሄደው የተሽከርካሪ የመንገድ ላይ ክትትል እና ድጋፍ አፈጻጸም ተገመግሟል።

በ 22 የተሽከርካሪ ቴክኒክ ምርመራ ተቋማት፣ በ 31 የከተማ ትራንስፖርት ተርሚናሎች እንዲሁም 9 በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ላይ ድንገተኛ ፍተሻ መካሄዱ በግምገማው ተገልጿል።

ለዘጠኝ ቀናት በአዲስ አበባ እና በሸገር ከተማ በተለያዩ መንገዶች በተካሄደው የመንገድ ላይ ክትትል አና ድጋፍም በአሽከርካሪዎች እና በተሽከርካሪዎች ላይ በርከታ ጉድለቶች መታየታቸውን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ደኤታ አቶ በርኦ ሀሰን ገልፀዋል።

በተደረገው ክትትል እና ድጋፍም የተሽከርካሪ የቴክኒክ ብቃት ሁኔታ ሳያሟሉ ቦሎ ያላቸው ተሽከርካሪዎች መኖራቸው፣ እንደ ሀገር ወጥ የሆነ ታሪፍ ቢኖርም ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉ መኖራቸው ከተገኙ ጉድለቶች መካከል ተጠቅሰዋል፡፡

እንዲሁም ተሽከርካሪው ከመጫን አቅሙ በላይ ትርፍ ጭነት የሚጭኑ አሽከርካሪዎች መኖራቸው እና በአንዳንድ አሽከርካሪዎች ተደራራቢ የትራፊክ ቅጣት ያላቸው መሆኑም ተገምግሟል፡፡

በቀጣይ የሚታዩ ቸግሮችን ለመቅረፍ እንዲቻል ዘላቂነት ያላቸው ስራዎች እንደሚሰሩ ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል፡፡

ይህም የተሽከርካሪ መርማሪ ተቋማትም ሆነ የአሽከርካሪ ማስልጠኛ ተቋማት ከተለመደው አሰራር ውጭ በቴክኖሎጂ በተደገፈ እና በዲጂታል ሲስተም ከማዕከል ቁጥጥር ለማድረግ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል፡፡

በድንገተኛ ፍተሻው ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በታዩ ክፍተቶች ላይ ለተቋማት በተሰጠ የግብዓት መነሻ በተለይ ልዩ ትኩረት የሚፈልጉ ተገልጋዮችን በመለየትና በግልጽ ጽፎ በመለጠፍ ማስተካከያዎች እየተወሰዱ መሆኑን መግለፃቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review