በየደረጃው የሚገኘው የፓርቲ አደረጃጀት የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ ይገባል- አቶ ሞገስ ባልቻ

You are currently viewing በየደረጃው የሚገኘው የፓርቲ አደረጃጀት የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ ይገባል- አቶ ሞገስ ባልቻ

በየደረጃው የሚገኘው የፓርቲ አደረጃጀት የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ ይገባል- አቶ ሞገስ ባልቻ

AMN – ጥር 13/2017 ዓ.ም

በየደረጃው የሚገኘው የፓርቲ አደረጃጀት የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ እና ሌብነት እና ብልሹ አሰራርን በመታገል ረገድ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ የብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ተናገሩ፡፡

የብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የ2017 በጀት አመት የስድስት ወራት የእቅድ አፈጻጸሙን ሲገመግም በዋነኛነት የፓርቲውን አቅም በማጠናከር የመንግስት ስራን ማሳለጥ በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ ትኩረት ተሰጥቶ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡

ብልጽግና ፓርቲ በአንደኛ መደበኛ ጉባኤው ካስቀመጣቸው ዋና ዋና የትኩረት መስኮች መካከል ጠንካራ ፓርቲ ለጠንካራ መንግስት መኖር ዋነኛ መሰረት በመሆኑ በየደረጃው ያለውን የፓርቲውን መዋቅር በማጠናከር የመንግስት ስራን ማቀላጠፍ አንዱ መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ተናግረዋል፡፡

በየደረጃው የሚገኘው የፓርቲ መዋቅር በተቋማት ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲቀላጠፍ መስራት እና የህዝብን እርካታ ማሳደግ እንደሚጠበቅበትም ነው ኃላፊው የተናገሩት፡፡

ሌብነት እና ብልሹ አሰራር አሁንም ተግዳሮት እንደሆነ የተናገሩት አቶ ሞገስ በየደረጃው ያለው የፓርቲ መዋቅር በጥብቅ ክትትል ይህንን ሊዋጋ ይገባልም ነው ያሉት፡፡

ሌብነት እና ብልሹ አሰራርን በመታገል ረገድ እንዲሁም በየደረጃው አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል ረገድ የፓርቲ መዋቅሮች ሚና ከፍተኛ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

በየደረጃው የፓርቲን አቅም በማጠናከር ለመንግስት አገልግሎት መሳለጥ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የግምገማው ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡

በበበጀት አመቱ ቀሪ ጊዜያት የመንግስት ስራን በብቃት የሚመራ የፓርቲ አደረጃጀትን ለማጠናከር ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም ነው አቅጣጫ የተቀመጠው፡፡

በሰብስቤ ባዩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review