በዩክሬን ጦርነት ዙርያ ከፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩ

You are currently viewing በዩክሬን ጦርነት ዙርያ ከፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩ

AMN-መጋቢት 6/2017 ዓ.ም

በዩክሬን ጦርነት ማስቆምን በተመለከተ ከሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተናግረዋል።

ፕሬዝደንቱ ይህንን ያሉት ፕሬዚዳንት ፑቲን እና የአሜሪካው ልዑክ ስቲቭ ዊትኮፍ ሀሙስ ዕለት በሞስኮ ተገናኝተው ከተወያዩ በኋላ ነው።

ይህንን ተከትሎ ዶናልድ ትራምፕ በትሩዝ ማኀበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት ጽሁፍ፣ ውይይቱ አደገኛውን እና ደም አፋሳሹን ጦርነት ለማስቆም ዕድል ይፈጥራል ብለዋል።

የኋይት ሐውስ የፕሬስ ሴክሬታሪ ካሮሊን ሌቪት በበኩላቸው፣ በሞስኮ በፑቲን እና በዊትኮፍ መካከል የተደረገው ውይይት አመርቂ እንደነበር ተናግረዋል።

ትራምፕ በፑቲን እና ሩሲያውያን ላይ ትክክለኛውን ነገር እንዲያደርጉ ግፊት አድርገዋል ማለታቸውንም ቢቢሲ አስነብቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review