በደብረ ብርሃን ከተማ በ1 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባ የመኪና ባትሪ ማምረቻ ፋብሪካ ተመረቀ

You are currently viewing በደብረ ብርሃን ከተማ በ1 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባ የመኪና ባትሪ ማምረቻ ፋብሪካ ተመረቀ

AMN_የካቲት 18/2017 ዓ.ም

በደብረ ብርሃን ከተማ በ1 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባ የመኪና ባትሪ ማምረቻ ፋብሪካ ዛሬ ተመርቋል።

ፋብሪካው የተገነባው ሲፋን ኒው ኢነርጂ ማኑፋክቸሪንግ በተሰኘ ድርጅት አማካኝነት ነው።

በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ- ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ይርጋ ሲሳይ፣ የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ እና የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት ተገኝተዋል።

በስድስት ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ፋብሪካው ተኪ ምርት በማምረት የውጭ ምንዛሪ ወጪን እንደሚያስቀር የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review