በገበያ ማዕከላቱ ጥራት ያላቸው ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እያገኘን ነው፡- ሸማቾች

You are currently viewing በገበያ ማዕከላቱ ጥራት ያላቸው ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እያገኘን ነው፡- ሸማቾች

AMN – ሚያዚያ 24/2017 ዓ.ም

በከተማዋ በተገነቡ ግዙፍ የገበያ ማዕከላት ጥራት ያላቸው ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እያገኙ መሆናቸውን ሸማቾች ተናገሩ፡፡

ነዋሪዎች የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በአቅራቢያቸው ማግኘት ይችሉ ዘንድ ዘመናዊ የግብይት ማዕከላት በተለያዩ የመዲናዋ መግቢያ በሮች ተገንብተው አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርጓል ፡፡

ይህም በከተማዋ የሚስተዋለውን የኑሮ ውድነትና አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪን መቆጣጠር ማስቻሉ ይነገራል፡፡

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በአቃቂና ለሚኩራ የግብርና የገበያ ማዕከላት ያለውን የምርት አቅርቦትና የግብይት ስርዓት ቅኝት አድርጓል፡፡

በገበያ ማዕከላቱ በቂ የምርት አቅርቦት መኖሩንም ባደረገው ቅኝት ተመልክቷል፡፡ ሸማቾችም የሚፈልጉትን ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ እየገዙ ስለመሆናቸው ተናግረዋል፡፡

የተለያዩ አትክልትና ፍራፍሬዎችን ጨምሮ የሰብል ምርቶችንና የእንስሳት ተዋፅኦችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቹ እያቀረቡ መሆናቸውን ነጋዴዎች ተናግረዋል፡፡

በከተማዋ ተገኘቡት የገበያ ማዕከላት የኑሮ ውድነትን እያረጋጉና ከዚህ በፊት ይስተዋል የነበረውን የደላላ ሰንሰለት ያስቀሩ መሆናቸውንም ሸማቾችና ነጋዴዎች ገልጸዋል፡፡

በማዕከላቱ ምርቶች በተወሰነላቸው ዋጋ እንዲሸጡና አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ እንዳይፈጠር ቁጥጥርና ክትትል እየተደረገ መሆኑን የየክፍለከተሞቹ የንግድ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ተናግረዋል፡፡

በመዲናዋ የመግቢያ በሮች የተገነቡ ግዙፍ የገበያ ማዕከላት የዋጋ ንረትን በማረጋጋትና የምርት አቅርቦትን አስተማማኝ በማድረግ ረገድ ጉልህ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ተከትሎ ተጨማሪ ሁለት የገበያ ማዕከላት በቅርቡ አገልግሎት መስጠት እንዲጀምሩ ከተማ አስተዳደሩ በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በሄለን ጀንበሬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review