በገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ የተመራ የልኡካን ቡድን ከቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ጋር ተወያየ

You are currently viewing በገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ የተመራ የልኡካን ቡድን ከቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ጋር ተወያየ

AMN – ጥር 16/2017 ዓ.ም

በገንዘብ ሚኒስትር አቶ አሕመድ ሽዴ የተመራ የልዑካን ቡድን ከቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ቼን ዢያኦዶንግ ጋር በቤጂንግ ተወያይቷል።

አቶ አህመድ በሚኒስትር ዴኤታው ጽ/ቤት ተገኝተው ያደረጉት ውይይት የሁለቱ ሀገራት መሪዎች እ.አ.አ 2023/24 ባደረጉት ውይይት በደረሱባቸው ስምምነቶች አተገባበር ላይ ያተኮረ ነው።

አቶ አሕመድ ሽዴ እና ሚስተር ቼን ዢያኦዶንግ በወቅቱ መሪዎቹ ለመተግበር የፈረሟቸው ስምምነቶች በፍጥነት ወደ ተግባር በሚሸጋገሩበት ሁኔታ ላይ ከመግባባት ላይ መድረሳቸው ተመልክቷል፡፡

በተለይም ሁለቱ መሪዎች በደረሱባቸው ስምምነት መሰረት በንግድ ፤ በኢንቨስትመንት፤ በመሰረት ልማት እና በሌሎች የልማት ትብብሮች ላይ የተደረሰው ስምምነት በሚተገበርበት ሁኔታ ላይትኩረት ሰጥተው መወያየታቸውን ቤጂንግ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review