በጋራ ሆነን የማንሻገረው ፈተና፣ የማናስመዘግበው ድል አይኖርም ሲሉ የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታ ገለጹ

You are currently viewing በጋራ ሆነን የማንሻገረው ፈተና፣ የማናስመዘግበው ድል አይኖርም ሲሉ የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታ ገለጹ

AMN – ግንቦት 18/2017 ዓ.ም

የየካ ክፍለ ከተማ በመዲናዋ በሚከናወኑ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ የልማት ስራዎች ለተሰማሩ አካላት ማእድ አጋርቷል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ብርሐኑ ረታ፣ በመዲናዋ የሚከናወኑ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ የልማት ስራዎች የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚከናወኑ ስራዎች አካል ናቸው ብለዋል።

ስራዎቹ የዜጎችን ህይወት የሚያሻሽሉ ናቸው ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው፣ በተለይም የወንዝ ዳርቻ ልማቶች ክረምት በመጣ ቁጥር የሚጨነቁ ዜጎችን ችግር በዘላቂነት የፈታ ነው ብለዋል።

በእነዚህ ስራዎች ታሪካዊ አሻራችሁን ያኖራችሁ አካላት ክብር ይገባችኋል ያሉት ዋና ስራ አስፈጣሚው፣ ስራዎቹ የሁሉንም የአስተዳደሩ ነዋሪዎችን ተሳትፎ የተቸረው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አቶ ብርሃኑ፣ በጋራ ሆነን የማንሻገረው ፈተና፣ የማናስመዘግበው ድል አይኖርም ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በሔኖክ ዘነበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review