በግማሽ ዓመቱ ከ 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ የዋጋ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል

You are currently viewing በግማሽ ዓመቱ ከ 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ የዋጋ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል

AMN-ጥር 18 /2017 ዓ.ም

በ2017 ግማሽ ዓመት ከ 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ የዋጋ ግምት ያላቸውን የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ከ3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ የዋጋ ግምት ያላቸውን የወጪ ገቢ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አስታውቀዋል።

በቁጥጥር ሥር ከዋሉት ዕቃዎች መካከል በርካታ ተሽከርካሪዎች፣ መድኃኒቶች በህገ-ወጥ መንገድ ሊወጡ የነበሩ የከበሩ ማዕድናት እንዲሁም በሰው ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድኃኒቶችንና ምግቦች እንደተያዙም ጨምረው ተናግረዋል።

በሌላ በኩል በድንበር አካባቢዎች በተደረገው ጠንካራ ቁጥጥርና ክትትል የአልሸባብ የሽብር ቡድንን ጨምሮ ሌሎች የሽብር ኃይሎችን በመከላከል ረገድ የታየው ብቃት ጠንካራ የፖሊስ ኃይል በተቋሙ እየተገነባ መምጣቱን አንስተዋል።

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እየታገዘ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በግማሽ ዓመቱ ታላላቅ ሀገራዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ሁነቶች ያለ ምንም የፀጥታ ችግር በስኬት መጠናቀቃቸው ለቀጣይ የተልዕኮ አፈፃፀም ልምድ የተወሰደባቸው መሆኑንም መግለጻቸውን ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review