AMN – ጥር 7/2017 ዓ.ም
በጎንደር ከተማ እየተካሄዱ ያሉት የፋሲለደስ እድሳት እና የኮሪደር ልማት ሥራዎች እድገት እጅግ አበረታች ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት በሥራው ለተሳተፉ ሁሉ በተለይም በክብር ለተሞሉት እንግዳ ተቀባይ የጎንደር ነዋሪዎች በሙሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን ለመግለጽ እወዳለሁ ብለዋል።