በጎዴ እየተካሄደ ያለው ለውጥ አበረታች ነው፡-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN – ታኅሣሥ 25/2017 ዓ.ም

በጎዴ እየተካሄደ ያለው ለውጥ አበረታች ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት ከሁለት ዓመታት በፊት ወደ ጎዴ መጥቼ ነበር ብለዋል።

ከዚያ ወዲህ እየተካሄደ ያለው ለውጥ አበረታች ነው ሲሉ አመልክተዋል።

በጽኑ ሃሳብ ማተኮር ያለብን በልማት ላይ ነውያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይኽ መንገድ ለእድሎች በር የሚከፍት፣ የሕይወት ደረጃን የሚያሻሻልና ማኅበረሰብን የሚያሻግር ጎዳና ነው ሲሉ ገልጸዋል።

በምዕራብ ጎዴ የመስኖ ፕሮጀክት በተለየ ደስታ ተስምቶኛል ብለዋል።

በአንድ ወቅት ገላጣ የነበረው በረሃማ መሬት በመስኖ አሁን ታርሶ በተስፋ ሰጪ አቅም የሰሊጥ፣ ስንዴ፣ በቆሎ አዝርዕት ምርት እና በተለያዩ የፍራፍሬ ምርቶች የተሞላ ስፍራ ሆኗል ሲሉ ተናግረዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review