በፓኪስታኗ ላሆር ከተማ በአየር ብክለት ሳብያ ትምህርት ቤቶች ተዘጉ

You are currently viewing በፓኪስታኗ ላሆር ከተማ በአየር ብክለት ሳብያ ትምህርት ቤቶች ተዘጉ

AMN – ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም

በፓኪስታን ላሆር ከተማ የአየር ብክለት ከፍተኛ ደረጃ ላይ በመድረሱ በከተማዋ የሚገኙ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሙሉ ለአንድ ሳምንት እንዲዘጉ አስገድዷቸዋል፡፡

በተጨማሪም “ግሪን ሎክዳውን” በሚል በተወሰደ ርምጃ በከተማዋ 50 በመቶ የሚሆኑ የቢሮ ሰራተኞች ከቤት ሆነው ስራቸውን እንዲያከናውኑ ተወስኗል።

የፑንጃብ ከፍተኛ ሚኒስትር የሆኑት ማሪያም አውራንዘብ፣ አሁን በከተማዋ ያለው ጭጋግ ለልጆች በጣም ጎጂ መሆኑን በመግለጽ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችም ጭምብል ማድረግ ግዴታ መደረጉን ጠቁመዋል፡፡

ባለስልጣናት የከተማዋ ነዋሪዎች ከቤት እንዲቆዩና አላስፈላጊ ጉዞ ከማድረግ እንዲቆጠቡም አሳስበዋል፡፡

የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው፣ መርዛማ አየር መተንፈስ በአንጎል ውስጥ ደም መፍሰስ፣ ለልብ ሕመም፣ ለሳንባ ካንሰርና አንዳንድ የመተንፈሻ አካላት በሽታዎችን ጨምሮ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል።

የፓኪስታን ሁለተኛ ትልቅ ከተማ የሆነችው ላሆር ለሁለተኛ ጊዜ በዓለማችን እጅግ የተበከለ አየር ካላቸው ከተሞች ዝርዝር ውስጥ በአንደኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን ቢቢሲ አስነብቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review