በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት ታጣቂዎችን በአስቸኳይ ትጥቅ በማስፈታት ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ማድረግ እንደሚያስፈልግ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ገለጹ

You are currently viewing በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት ታጣቂዎችን በአስቸኳይ ትጥቅ በማስፈታት ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ማድረግ እንደሚያስፈልግ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ገለጹ

AMN ግንቦት 30/2017

በትግራይ ክልል የቀድሞ ታጣቂዎች የተሀድሶ ስልጠና እንዲወስዱ መደረጉ፣ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦትና የመልሶ ግንባታ ስራዎችም የሰላም ስምምነቱ ተግባራዊ ውጤት ተደርገው የሚወሰዱ መሆናቸው በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ሂደት የተገኙ ስኬቶችን አስመልክቶ በየካቲት 2017 ዓ.ም የአፈፃጸም ሪፖርት ላይ ውይይት በተደረገበት ወቅት መገለጹ ይታወሳል።

በፌዴራል መንግስት ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በኋላ በክልሉ ባንክ፣ አየር መንገድ እና ስልክን ጨምሮ ሌሎች በርካታ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሥራ በፍጥነት እንዲጀመሩ መደረጋቸው፣ መሰረተ ልማቶች መልሰው መገንባታቸው ሕዝቡ የሰላም ስምምነቱን ውጤት እንዲያይ አድርጓል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከወራት በፊት በሰጡት ማብራሪያ፤ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረተ ልማቶችን በመመለስ የትግራይ ህዝብ አገልግሎት እንዲያገኝ ማድረግ መቻሉን በመጥቀስ ሀሳቡን አጽንኦት ሰጥተውታል።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የፕሪቶርያ ስምምነት በትግራይ ክልል የነበረውን ጦርነት በማስቆም ረገድ የተጫወተውን ሚና አድንቀዋል፡፡

በትግራይ ክልል ተደጋጋሚ ጉብኝት በማድረግ የሰምምነቱን ትግበራ መመለከታቸውን የገለጹት አምባሳደር ማሲንጋ፤ አሁንም ስምምነቱን በተሟላ መንገድ በመተግበር በኩል ብዙ የሚቀሩ ተግባራት መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡

አምባሳደሩ እንደገለጹት፤ በትግራይ ክልል ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የፕሪቶሪያውን ስምምነት በተሟላ መንገድ መተግበር ይገባል ማለታቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የቀድሞ ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ በቅርቡ በሰጡት መግለጫ፤ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አተገባበር ተፈናቃዮችን የመመለስና ታጣቂዎችን መልሶ የማቋቋም ሂደት የተስተጓጎለው በራሳችን የውስጥ ሽኩቻ ነው ማለታቸው ይታወሳል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review