6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ በ24ኛ መደበኛ ጉባዔው የትምህርት ሚኒስቴርን የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ገምግሟል፡፡
የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የሚንስቴር መስርያ ቤታቸውን ሪፖርት ለምክር ቤቱ ያቀረቡ ሲሆን በኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት ስር ነቀል ለውጥ በማምጣት የሪፎርም ስራዎችን ለማሳካት ሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላትንና የማህበረሰቡን ድጋፍ እንደሚጠይቅ አብራርተዋል፡፡
የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል፣ የመምህራንን አቅም በማሳደግና በሌሎችም የአጠቃላይና ከፍተኛ ትምህርት ዘርፎች የተጀመሩ ሪፎርም ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ፕሮፌሰር ብርሃኑ ጠቅሰዋል።
በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ምንም ተማሪ ያላሳለፉ 700 ትምህርት ቤቶችን ለማብቃት ትምህርት ሚኒስቴር እቅድ ይዞ እየሰራ መሆኑንም መጠቆማቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡