በ2017 የውድድር ዘመን ሻምፒዮን ለመሆን ተዘጋጅተናል- የመቻል ሴት እግር ኳስ ተጫዋቾች

You are currently viewing በ2017 የውድድር ዘመን ሻምፒዮን ለመሆን ተዘጋጅተናል- የመቻል ሴት እግር ኳስ ተጫዋቾች
  • Post category:ስፖርት

AMN-ጥቅምት 20/2017 ዓ.ም

በ2017 ዓ.ም የውድድር ዘመን ለደረጃ ሳይሆን ሻምፒዮን ለመሆን መዘጋጀታቸውን የመቻል ሴት እግር ኳስ ተጫዋቾች ተናገሩ።

የመቻል ሴቶች እግር ኳስ ክለብ በ2016 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመን ጠንካራና ተፎካካሪ ከነበሩ ክለቦች መካካል አንዱ ሲሆን በሊጉም አራተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡

ክለቡ ዘንድሮ አዳዲስ ልምድ ያላቸዉን ተጫዋቾች ወደ ቡድኑ በማምጣት እና አዲስ አሰልጣኝ በመቅጠር ለ2017 የውድድር ዘመን ጠንካራ እና ሻምፒዮን ለመሆን በማሰብ ወደ ቅድም ዝግጅት ከገባ ከአንድ ወር በላይ አስቆጥሯል፡፡

ወደ ልምምድ ከገቡ ከአንድ ወር በላይ መሆኑን እና በሳምንት ስድስት ቀን ጠንካራ ልምምድ እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዘንድሮ የክለቡ ድጋፍና ክትትል ከአምናዉ የተሻለ መሆኑን የተናገሩት ተጫዋቾቹ ከራሳቸዉ የሚጠበቅባቸዉን ለማድረግ እና ለደረጃ ሳይሆን ለሻምፒዮን እንደተዘጋጁ ገለጸዋል፡፡

ዘንድሮ ወደ ክለቡ የመጣዉ እና አምና በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመቻል ወንዶች ከ20ዓመት በታች ቡድን ጋር ስኬታማ ጊዜን ያሳለፈዉ አሰልጣኝ መቶ አለቃ አብዱ ሞሃመድ በበኩላቸው፣ አዳዲስ ተጫዋቾችን ከነባሮች ጋር በማዋሃድ ቀድመዉ ወደ ልምምድ የገቡ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ክለቡ ካለፉት ዓመታት የተሻለ ዉጤት ለማስመዝገብ እየተዘጋጁ መሆንም ጠቁመዋል፡፡

በአዲሱ መንገሻ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review