ከታይታኒክ አደጋ በህይወት በተረፉ ኮሎኔል የተጻፈ ደብዳቤ እንግሊዝ ውስጥ በ3 መቶ ሺህ ፖውንድ በጨረታ ተሽጧል።
ደብዳቤው የተጻፈው ከታይታኒክ አደጋ በህይወት ከተረፉ ሰዎች ውስጥ አንዱ በሆኑት ኮሎኔል አርክባልድ ግራሲ ነው።
ኮሎኔሉ ታይታኒክ ጉዞ በጀመረችበት ዕለት ሚያዚያ 10 ቀን 1912 የጻፉት ይህ “ትንቢታዊ” ደብዳቤ ፤ “በዚህ ድንቅ መርከብ ላይ ፍርድ ከመተላለፉ በፊት የጉዞዬ ፍጻሜ እንዲሆን እጠብቃለሁ” ይላል።
እንግሊዝ ውስጥ ለጨረታ ቀርቦ ማንነቱ ባልታወቀ ባለሐብት በ3 መቶ ሺህ ፓወንድ የተገዛው ደብዳቤው ቅድሜያ ተሰጥቶት የነበረው ከፍተኛ የመሸጫ ዋጋ ግምት 60 ሺህ ፖውንድ እንደነበር ቢቢሲ አስነብቧል።