ቢል ጌትስ 99 በመቶ ሀብቴን ለበጎ አድራጎት አውለዋለሁ አለ

AMN- ግንቦት 1/2017 ዓ.ም

የማይክሮሶፍት ኩባንያ መሥራቹ ዕውቁ ባለጸጋ ቢል ጌትስ፣ 99 በመቶ ሀብቱን ለበጎ አድራጎት እንደሚያውለው አስታውቋል።

ቢል ጌትስ 1 በመቶ ሀብቴ ሲቀር ሌላው ለዓለም የድህነት ቅነሳ እንዲሁም ለትምህርት እና ለጤና ተቋማት መስፋፋት ይውላል ብሏል።

108 ቢሊየን ዶላር የተጣራ ሀብት ያለው ባለጸጋው ፣ ይህን ሀብቱን ለበጎ አድራጎት የማውረስ ቃሉን በቀጣዮቹ 20 ዓመታት በየደረጃው እንደሚጽም ይፋ አድርጓል።

ቃሉም በጌትስ ፋውንዴሽን በኩል እስከ 2045 ድረስ ተግባር ላይ እንደሚውል መናገሩን አል ጃዚራ ዘግቧል።

የ69 ዓመቱ የፈጠራ ሰው ቢል ጌትስ ከማይክሮሶፍት በተጨማሪ ሊንክደን፣ ዋልማርት፣ ካተር ፒለር እና ፌድ ኤክስን ጨምሮ ከ10 የሚበልጡ ግዙፍ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ባለቤት ነው።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review