ቢሮው በምሽት የንግድ እና የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጥ የወጣውን ደንብ ተግባራዊ ማድረግ ጀመረ

You are currently viewing ቢሮው በምሽት የንግድ እና የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጥ የወጣውን ደንብ ተግባራዊ ማድረግ ጀመረ

AMN – መጋቢት 10/2017

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ በምሽት የንግድ እና የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ የወጣውን ደንብ ቁጥር185/2017 ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን አስታወቀ።

ቢሮው የአዲስ አበባ ከተማ አሁን ከደረሰችበት ኢኮኖሚያዊና ማህበረሰባዊ ለውጥ አንፃር የአብዛኛው ማህበረሰብ የሥራ ባህል እና ፍላጎት በመለወጡ የንግድ ሥራዎችንና አገልግሎቶችን በምሽት መከወን እየተለመደ የመጣውን ተግባር ወጥነትና ቀጣይነቱን ማረጋገጥ ማስፈለጉን አንስቷል፡፡

በመሆኑም በከተማዋ በስፋት እየተከናወነ የሚገኘው መሠረተ-ልማት በኢኮኖሚው ላይ የፈጠረውን መነቃቃት አጠናክሮ ለማስቀጠል፣ የስራ ባህልን ይበልጥ ለማዳበር ፣ የኢኮኖሚ እድገትን ለማፋጠን፣ የከተማዋን ተወዳዳሪነት እውን ለማድረግ ቀን ከሚሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ በምሽት የንግድ እና አገልግሎት መስጫ ተቋማት አገልግሎት የሚሰጡበት ምቹ ሁኔታ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን ገልጿል፡፡

ለዚህም ደንቡ መውጣቱን አንስተው ይህ ደንብ ቀደም ብሎ የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ያስተላለፈውን ውሳኔ ለማስፈጸም በመሆኑ ከዛሬ መጋቢት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩን የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ሐቢባ ሲራጅ አብራርተዋል፡፡

በደንቡ የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች ማብራሪያ በሁሉም የሚዲያ አውታሮች አማካኝነት ማህበረሰቡ እንዲያውቃቸው እንደሚደረግ እና ደንቡን የማስተዋወቅ ስራ እንደሚሰራም መግለፃቸውን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review