ባህርዳርን ወደ ምቹ ከተማነት ለማሸጋገር የሚረዱ የመንገድ ግንባታ፣ የኮሪደር ልማት እና የተቋማት ዕድሳት ስራዎች በከፍተኛ ርብርብ እየተከናወኑ መሆኑን ተመልክተናል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገልጸዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ዛሬ በከተማዋ ተገኝተን እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተናል ብለዋል፡፡
ከተማይቱን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ለቱሪስቶች ተወዳጅ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ከተማዋ ለሚመጡ እንግዶች ደግሞ ተመራጭ መዳረሻ ለማድረግ እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎች ይበሉ የሚያሰኙ መሆናቸውንም አንስተዋል፡፡
እነዚህ የተጀመሩ መልካም ተግባራትን ተጠናክረው እንዲቀጥሉ፣ በተጨማሪም ፕሮጀክቶችን በጥራት ለማጠናቀቅ እየተደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ጠቁመዋል።
መንግስት የከተሞች ውበት እና የተፈጥሮ ሀብት ተጠብቆ እንዲዘምኑና የቱሪስት መስህብነታቸው እንዲጨምር ክትትል እና ድግፍ ለሚሹ ጉዳዮች አስፈላጊውን ድጋፍ እና ክትትል ያደርጋል ሲሉም አያይዘው ገልጸዋል፡፡