AMN-የካቲት 12/2017 ዓ.ም
ባለፉት ስድስት ወራት 546 ሺ 443 የውጪ ሀገር ቱሪስቶች ከተማዋን መጎብኘታቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ፡፡
እየተካሄደ ባለው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ሪፖረታቸውን ያቀረቡት ከነቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት እያካደ ባለው የ2017 ዓ.ም 4ኛ የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤው የ6 ወራት የሥራ አፈፃፀም እየገመገመ ይገኛል፡፡
አፈጻጸሙን ያቀረቡት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበጀት አመቱ 4 ሚሊዮን 424 ሺ 62 የሀገር ውስጥ እና 546 ሺ 443 የውጪ ሀገር ቱሪስቶች ከተማዋን መጎብኘታውን አስታውቀዋል፡፡
በዚህም ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ቱሪስቶች 96 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በከተማ የኢንቨስትመንት ፍሰቱን ከማሳደግ አንጻርም ቀልጣፋ አገልግሎት ለማቅረብ በተደረገው ጥረት አመርቂ ዉጤት መመዘገቡንም አክለዋል፡፡
በዚህም ለ1 ሺ 303 ባለሀብቶች አዲስ፣ ለ151 ባለሀብቶች ማስፋፊያ፣ ለ75 ባለሀብቶች ምትክ እና ለ191 ባለሀብቶች ለውጥ/ማሻሻያ ኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን ጠቁመዋል፡፡
ለ1008 ባለሃበቶች ደግሞ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ዕድሳት መስጠት መቻሉን ተናገረዋል፡፡
በተጨማሪም ከተማዋን በባህል እና ቱሪዝም ተወዳዳሪነቷን ከመፍጠር አንጻር፣ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎችም እየሰፉ በመሄዳቸው የቱሪስት ፍሰቱን የሚያሳደጉ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛልም ብለዋል ከንቲባዋ በሪፖርታቸው፡፡
በወርቅነህ አቢዮ