ባለፉት ስድስት ወራት ግምታቸው ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የተበላሹ ምግብና ጤና ነክ ምርቶች መወገዳቸው ተገለፀ

You are currently viewing ባለፉት ስድስት ወራት ግምታቸው ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የተበላሹ ምግብና ጤና ነክ ምርቶች መወገዳቸው ተገለፀ

AMN – ጥር 5/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ መድሀኒትና ቁጥጥር ባለስልጣን ባለፉት ስድስት ወራት ግምታቸው ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የተበላሹ ምግብና ጤና ነክ ምርቶች መወገዳቸውን አስታወቀ

በጉዳዩ ዙሪያ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሙሉእመቤት ታደሰ ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥተዋል ፡፡

ዋና ስራ አስኪያጇ ወ/ሮ ሙሉእመቤት የአደባባይ በዓል በሆነው የጥምቀት በዓል ማህበረሰቡ የተለያዩ ምግቦችን ከገበያ ሲሸምት ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት ገልፀዋል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱም የቁጥጥርና ክትትል ስራውን እየሰራ ስለመሆኑ አብራርተዋል።

ባለፉት ስድስት ወራት በተደረገው ቁጥጥር የተለያዩ ችግሮች በተገኙባቸው 466 ተቋማት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ስለመውሰዱ የባለስልጣኑ የክትትል ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ እንጋ እርቀታ ገልጸዋል ፡፡

በዚህም የዋጋ ግምታቸው ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ምግብና ጤና ነክ ምርቶች እንዲወገዱ ስለመደረጉም አብራርተዋል ።

በፅዮን ማሞ

All reactions:

35በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን and 34 others

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review